Sunday, December 1, 2013

በዜጎቻችንን መነገድ ተገቢ አይደለም

              ጭፍን የሆነ ድጋፍም ሆነ ተቃወሞ ተገቢ አይደለም ብለው ከሚያምኑ ሰዎች መንደር ነኝ. ያው ሰሞነኛ ወሬው ሳውዲ በመሆኑ እኔም እዛው አካባቢ እገኛለሁ. ይሄን ጉዳይ ለመከታተል የወያኔ መንግስት ደጋፊም ሆነ ተቃዋሚዎች ምን ይላሉ ብዬ  እዚህም እዚያም ለመመልከት ሞክሬ ነበር.                                                

ወያኔ መንግስት ደጋፊዎች                                                                          
መንግስት እያደረገ ያለውን ስራ ሰማይ ላይ በማድረስ በማሞገስ ላይ ይገኛሉ. ከውጭ ጉዳይ ተብዬው የቲውተር አድራሻ የሚወጣውን ቁጥር እያባዙ የቁጥር ጫወታ መጀመራቸው የሚያስተዛዝብ ብቻ ሳይሆን ወደ ፊት የሚያጠያይቅም ጭምር ነው. በነገራችን ላይ ደጋፊዎች መንግስታችን 40፣50፣60 ሺ ወደ አገር አስመለሰ በማለት እንደ ስኬት ማውራቱና ማሞገሱ ተገቢ ነው ብላቹ ካሰባቹ እነዚሁ ሰዎች በፖለቲካዊም ሆነ በኢኮኖሚአዊ ችግራቸው ከሀገር ለመውጣታቸው የመጀመርያው ተጠያቂው ማን ነው? ያኔ ምነው ይሄ ሁሉ ወጣት ከሀገሩ ሲሰደድ ዝምታን መረጣችሁ? ትላንትና አገራችን እያደገች ነው የሚሰደድ ሰው የለም ስትሉ አልነበረም እንዴ? ዛሬ ታድያ ይሄ እናንተው የምትጠሩት ቁጥር ታዲያ ምን ይነግራቹ ይሆን?                                              
ለማንኛውመ ወንድሞቻችን ዛሬም እንደ ትላንቱ  ስደትን የሚመርጡበትን ምክንያት በመረዳት ስደት በቃ በሉ እላለሁ. ወንድሞቼ ስደተኞችን አስመልክቶ መንግስት ተብዬውን ልትጠይቁት የሚገባ በርካታ ነገሮች አሉ. ማስታወስ ካስፈላገ መጠቆመ ይቻላል. 

                                                                                    
1.በኤጀንሲ ስም ሀገራችን ወስጥ ቁጭ ብለው ዘመናዊው የባርነት ንግድን  ከከተማዎች    አንስቶ ገጠር ድረስ የዘለቀ ንግዳቸውን እያደሩት ያሉት እነማን ናቸው? 

2. በህገ ወጥ መንገድ ዜጎችንን በሱዳን ፣ በሱማሌ ፣ በጅቡቲ አውጥተው በባሕርና በበረሃ ለሞትና ለስቃይ ዳርገው በሰው ደም እየከበሩ ያሉት እነማን ናቸው? 
          
3. ዜጎችን በሲና በረሃ አስረው ሲያበቁ ከደሃው ገበሬ ላይ የልጆችህ ማስፈቻ እያሉ በሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ እየተረከቡ ያሉትስ እነማን ይሆኑ? 

4.  በየትኛውም መንገድ በስደት በደረሰባቸው አገሮች ሁሉ በየኤምባሲዎች ተሰግስገው     በተለያየ መንገድ የስደተኛውን ገንዝብ ለመቦጥቦጥ እጃቸውን ታጥበው የተቀመጡት      የጥቂቶች አገልጋይ እነማን ናቸው? 
                                                         
5. የሳውዲ አፍጥጦ ስለመጣ እንጂ የታወቀው በየሃገሩ ኤምባሲ በቁም ያሉት አብደው የሞቱት ደግሞ ሬሳቸውን እንኳን ማን ይላከው?   

ከዚህ ጋር በተገናኘ መጠቆም የምፈልገው ነገር ቢኖር ከሳውዲ የሚመለሱ ዜጎችን በሚደረገው ጥረት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ጥረት ኢቲቪ አንደሚነግረን አለመሆኑን እኔ እንኳን ከቦታው ባሉ ሰዎች ለማጣራት ችያለሁ. የተመላሾችን የትራንሰፖረት ወጭ በሳውዲ መንግስት እየተሸፈነ ይገኛል ፣ IOM የሚባለው ድርጅት ቀላል የማይባል የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ይታወቃል.  በሌላ መለኩ የኢትዮጵያ መንገስት በዚህ የጭንቅ ቀን እንኳን በሊሴ ፓስ ሰበብ ከ400 ርያድ ጀምሮ ገንዘብ በመሰብሰብና ለስርዓቱ ደጋፊዎች ቅድሚያ በመስጠት መሰሪ ስራ ላይ ተጠምደው ይገኛሉ. በሞት አፋፍ ላይ ባለ ሕዝብ ላይ እነዲህ ያለ ስራን መስራት ምን የሚሉት ድንቁርና ነው. በአለም ዙርያ ያሉ ኤምባሲዎቻችን ውስጥ የሚሰራው ሸፍጥ የሚያቆስል ቢሆንም በእኔ አቅም እንኳን የተመለከትኳቸውን ወደ ፊት  በዝርዝር በሌላ ጊዜ ለማቀረብ እሞክራለሁ.                                                             

ከዚህ በላይ በ5 ነጠብ ለመጠቆም የሞከርኳቸው መልስ ከሚያሻቸው በርካታ ጥያቄዎች ጥቂቶቹ ናቸው.      

No comments:

Post a Comment