ላለፉት ሁለት ሳምንታት የምንሰማው እና የምናየው ሰቆቃ ቀላል አይደለም. አሁንም የሳውዲ ሰቆቃ ከመጨመሩም በላይ ተጠናክሮ መቅጠሉ ይሰማል. አብዛኛው ዜጋ ላለፉተ 20 አመት ከደረሰበት ችግር እና ስቃይ በላይ የወያኔ መንግስት ሚድያዎቹን እየተጠቀመ የሚሳለቅበት የከፋ ጎድቶታል. ዛሬም በወንድሞቻችን እና በእህቶቻችን ሞት ላይ ቁማር የሚጫወቱ ይመስለኛል. የወያኔ መንግስት ከጅመሩ እንደለመደው ጥቂቶች ብሎ ሲቀልድ እነዳለነበር ዛሬ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ኤምባሲ እና በተለያየ የውጭ ሚዲያዎች ላይ ባደረጉት ከፍተኛ ተቃወሞ በሳውዲም ሆነ በኢትዮጵያ መንገስት ላይ ቀላል የማይባል ጫና መፍጠሩ የታወቃል. በነገራችን ላይ በምኖርበት አገር እንግሊዝ በተደረገው ደማቅ እና ታሪካዊ ሰልፍ ላይ ተገኝቼ ያየሁትን ኢትዮጵያዊነት ሁሌም በማንነቴ እንድኮራ አድርጎኛል እነ አቦይ ስብሃት ገደልነው ያሉትን ኢትዮጵያዊነት በአለም ዙርያ ሲያበራ ከማየት በላይ የሚያስደስት ምንም ነገር የለም. ይሄ ኢትዮጵያዊነት ደግሞ በሰለፍ ብቻ የሚያበቃ መሆን የለበትም በምንችለው መጠን ሁሉ በዘር ፣ በሃይማኖት ሳንከፋፈለ ወገኖቻችንን እንታደግ ዘነድ በፈጣሪ ስም አሳስባለሁ. አምላክ ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይጠብቅ
No comments:
Post a Comment