ሀገራችን ከእስልምና ጋር ያላትን ዝምድና እንኳንስ ሙስሊሙ እኔም ሙስሊም ያልሆንኩት ከልጅነቴ ጀምሬ ጠንቅቄ አውቃለሁኝ. አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ለዚህ እንግዳ አይደለም. ለኢትዮጵያዊ ይህን ማውራት ለቀባሪው ማርዳት ማለት ነው. በረግጥ ማንኛውም ነገር ጊዜና ቦታ እንደሚወስነው መዘንጋት የለብንም. እንደሚታውቀው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላለፉት 2 ዓመታት ድምጻችን ይሰማ ብለው በተቃውሞ ላይ ይገኛሉ. ይህንን ተቃውሟቸውን በርካታ ክርስቲያኖቹም መደገፋቸው ይታወቃል. በተለይ በውጭ የሚገኙ የክርስትና አባቶች ከሙስሊም ወንድሞቻቸው ጋር ባደባባይ ሲመሰከሩ ታዝበናል. ይህንንም በአውዲዮም ሆነ በቪድዮ የተደገፈ ማስረጃዎች በተያየ ቦታ ስለሚገኝ መመልከት ይቻላል. በርግጥ ይህንን እንደ መንደርደሪያ የተጠቀምኩበት ለዛሬው ጽሑፌ ይረዳኛል ብዬ ነው.
ከዚህ ቀደም በተያዩ ድሕረ ገጾች የድምጻችን ይሰማን ጥያቄን አስመልከቶ ከፍተኛ ውይይት ሲደረግ ተመልክቼ ነበር. የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ጥያቄ በጥርጣሬ የሚመለከቱ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ከነበረው የጦፈ ውይይተ መረዳት ይቻላል. እኔም ጉዳዩን በጥንቃቄ መታየት አለበት የሚል አቋም ነው የነበረኝ. በዚህም የተነሳ አቋሜን ለራሴ ይዤው ነበር. ይሁንና በሳውዲ የሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው አስከፊ ወንጀል የተነሳ ዝምታዬን መስበር እንዳለበኝ ተረዳሁ.
ሳወዲ ወስጥ እየተደረገ ያለው ጭካኔ የተሞላበት አረመኔያዊ ተግባር ያላሳዘነው ኢትዮጵያዊ ይኖራል ብዬ አላስብም ነበር. አርብ እለት ማታ ግን አንድ ወዳጄ በኢሜል አድራሻዬ አንድ አውዲዮ እንዳዳመጥ ይልክልኛል. አውዲዮው የተቀዳው በፓልቶክ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መወያያ መድረክ ውስጥ ነው. የተቀዳበትን ጊዜ ባላውቅም ከይዘቱና ከውይይቱ በርግጠኝነት መናገር የምችለው ግን ባሳለፍነው ወር ውስጥ ነው.ምክንያቱም የውይይቱ ዋናው አጀንዳ በሳውዲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አስመልክቶ ነበር. እውንት ለመናገር ከተባለ በሳውዲ እይተደፈሩ ፣ እየተደበደቡ ፣ አልፎም እየሞቱ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን በሙሉ ኃይማኖት ፣ ዘር ፣ ጾታ ሳይጠየቅ በጅምላ ሆኖ ሳለ በማንኛውም መመዘኛ በኃይማኖታዊም ይሁን በፖለተካዊ የሳውዲ መንግስትን እርምጃ የሚደግፍም ሆነ በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖች የሚያሳጣ አካል ከሳወዲዎች ለይተን አንመለከተውም.
የትኛውም ወንጀል ተሰርቶ ከሆነ በህግ ሊጠየቁ ይገባል እንጂ ዘይት ጠጥቶ በጠገበ አረብ ሊደፈሩ ፣ ሊደበደቡ ወይም ሊገደሉ አይገባም. ሳውዲዎች ባላቸው ሚድያ ተጠቅመው እየቀቡን ያለውን ጥላሸትም ሆነ የሚሰጡትን ማሰተባበያ በቂ ሆኖ ሳለ ወገኖቻችን ከምንላችሁ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ይህንን መስማት ግን ያማል በርግጥም በጣም ያማል. ወገኖቼ ዛሬ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያዊነት መዋረዱን መመለከት የለባችሁም የምንሞትላት የምትሉትን እስልምናን ጠብቃ ዛሬ ላላችሁበት ያበቃች ሃገር ልጆች መሆናችንን አትዝንጉ.
ለእስልምና ከኢትዮጵያ የበለጠ ባለውለታ የላትም. እጅ አመድ አፋሽ መሆንም ተገቢ አይደለም. እዚህ ጋር ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በሙሉ እነዲህ ያስባሉ ብዬ አልገምትም. ነገር ግን ይህን ሃሳብ እያራመዱ ያሉት እነማን እንደሆኑ አጋልጦ ማውጣቱ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን የሚመለከት ጉዳይ ነው. ይህን ማድረግ ደግሞ ግዴታቸሁም ጭምር ነው. እስልምና ሰላም ብቻ ሳይሆን ፍትህም መሆኑን አምናለሁ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ኢፍትሃዊ ተግባር እስልምና እንደሚያወግዝ ሁሉ ኢስላሞችም ይንን ሊያወግዙና እውነተኛውን ፣ ሃቀኛውን ፣ ፍትህ የተሞላበትን እስልምናን ሊያሳውቁን እንጂ ይሄን አሁን እየተወራ ያለውን አስነዋሪ እና አሳፋሪ
ተገባራችሁን በአስቸኳይ ልታቆሙ ይገባል.
ማሳሰቢያ በመላው አለም ከ40 ከተሞች በላይ በተደረገው ታላቅና አስገራሚ ሰልፍ ላይ ዘር ፣ ኃይማኖተ ፣ እድሜ እና ጾታ ሳትለዩ ለወጣችሁና አሁንም እየወጣቸሁ ለምትጮሁ ወገኖቼ በሙሉ ያለኝን አደናቆት መግለጽ ወዳለሁ. የወገኖቻችን ስቃይና መከራ እስከሚያበቃ ድረስ ልክ እንደዚሁ እጅ ለእጅ ተያየዘን መጮህ አለብን በዘር ፣ በኃይማኖተ ፣ በፖለቲካዊ አመለካከታችንም ሁነ በሌላ ሊለያዩን የሚፈልጉንን ለንረሳቸው ይገባል.
እግዚአብሔር አምላክ ሃገራችንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

No comments:
Post a Comment