Saturday, December 7, 2013

አራምባ እና ቆቦ

አራምባ እና ቆቦ
ይህንን ጽሑፍ ከመፃፌ በፊት ከራሴ ጋር ትንሽ ታግዬ ነበር, ምክንያቱም ሁለት የማይግናኙ ነግሮችን ለማመሳሰል መሞከር እንደ እብደት  ይቆጠራል እናም ዛሬ እኔም ትንሽ ላብድ ሳይሆን አይቀርም ነጭን ከጥቁር ላወዳድር ነው. ይህንን  ደግሞ ሳልፈልገውም ጭምር ነው. አንዳንድ  ብሎጎች ላይ የተመለከትኩት የተከበሩ የአፍሪካ አባት ማንዴላን ከአቶ መለስ ጋር ለማመሳሰል ያደረጉት ጥረት ሁለት ነገሮችን አሳይቶኛል.
  የመጀመርያው የሰዎቹን የዘቀጠ የአውቀት ደረጃ ሲሆን ሌላ ደግሞ ለተከበሩ ሰዎች ያላቸወን ንቀት ነውላልፉት በርካታ አመታት ያከበርናቸውን ስዎች ሲያዋርዱ ያምሰገናቸውን ሲያጣጥሉ  አለም የሸልማቸው ጋዜጦኞቻችንን በሆነው ባልሆንው ሰበብ ፍጥረው አስረው ሲያበቁ ዛሬ አዛኝ ቂቤ አንጓች ሲሆኑ ማየት ያስቃል. የማንዴላን ታሪክ ለመተረክ ብቃት ቢጠይቅም መለስና ማንዴላን የሚለያያቸውን ነገር ለይቶ ለማውጣት ግን ለኢትዮጵያዊ ቀላል ነው ብዬ አምናልሁ.

የማንዴላ ትግል
በሃገሩ የተስፋፋውን ዘርኝነት ለማጥፋት ፣ ፍትህና ዲሞክራሲን ለማስፈን ፣ እውነተኛ  እኩልነት ለማምጣት ፣ ስልጣንን ለሰፊው ሕዝብ ለመስጠት፣  ለተጨቆኑ , ፍትህ ላጡ ህዝቦች ፍትህን  ለማምጣት ፣ በአጠቃላይ መጥፎን አስወግዶ መልካም ለማስፈን የተደረገ ረጅምና  እልህ አስጨራሸ ትግል ነበር.

የመለስ ትግል
ከትግሉ መጀመርያ ጀምሮ አንድ የነበርች ሃገርን መከፋፍል ፣ ሀገሩትን  ከወታደራዊ  ወደ ዲክታተራዊ ሥርአት ለመውሰድ ፣ ስልጣን ለጥቂቶች  መፈንጫ ለማድረግ ፣ ዘርኛና ከፋፋይ የሆኑትን የቅኝ ገዢዎችን ስራ ለመቀጠል ጥቂቶቹ ሲሆኑ ሀገርን ከድጡ ወደማጡ ያስገባ ትግል ነው

ማንዴላ 27 ዓመት ለነጻነት ታስሯል
ማንዴላ ለህዝባቸው ነጻነት ሲታገሉ ለ27 ዓመት በእስር ቤት የቆዩ ብቻ ሳይሆኑ በእስር ቤት ቆይታቸው የህግ ዲግራያቸውን የተማሩ, ብቃታቸውን እዛም ሆነው ያስመሰከሩ, እስር ቤት ጥላቻን ሳይሆን ይቅርታ ያስተማራቸው እስር ቤት አካልን እንጂ ህሊናን እንደማያስር ለዘረኞች ያሳየ ወርቃማ ሰው
  
ስ ከ30 ዓመት በላይ ህዝባቸውን አስረዋል
ሀገር መምራት ሳይጀምሩ ከጫካ ጀምሮ ብዙዎች የአንድነት ሰዎችን በእስር ያሰቃዮ ለአንዳንዶች ጠባብ ለተቀረው ህዝብ ደግሞ ትልቅ እስር ቤት የሰሩ, ያሰብከውን መናገር የማይቻልባት ስርአት መስርተዋል.ጥቅት የማይባሉ ጋዜጠኞች, ፖለቲከኞች, የሰብዓዊ መብት ታጋዮች መኖሪያቸውን ቃሊቲ ካደረጉ ሰንብተዋል. ዛሬ በጅምላ የታሰረ ህዝብ ከሚገኝባቸ ሃገሮች የመጀመርያዎቹ አድርገውናል.

ማንዴላ የማይቻል ነገርን ችሎ አድርጎ አሳይቶናል
በሰው ልጅ የለውጥ ሂደት ውስጥ ትልቁን ቦታ የወሰዱት እንደ ማንዴላ የማይቻለውን ችለው ያሳዩ ሰዎች ናቸው. እንደ ማንዴላ ያሉ ሰዎች በክፍለ ዘመን የሚፈጠሩ እንቁዎች እንጂ እንደ መንገድ ላይ ቅጠል በየቀኑ የሚገኙ አይደሉም, ለዛም ነው አለም ለማንዴላ ክብር ያጎናጸፈው. በሕይወቱ እንዳከበረው ሁሉ በሞቱም እያሞገሰው ይገኛል. ሞቱን ሲመኙ ለነበሩ ይቅርታን ያደረገ  በዘመናችን እንኳንስ ለማድረግ ለማሰብ የማይቻልን መቻሉን በተገባር ያስመሰከረ ነው.

መለስ የነበረን እንዳልነበረ አፍርሰው አሳይተውናል
ለዘመናት ተቻችሉ ተከባቦ ተፋቅሮና ተዋዶ የኖረን ህዝብ በውስጡ የነበሩትን  የባህልና የኃይማኖት እሴቶች እንዳልነበር አውድመው አጥፍተው አንዱ ለአንዱ ለማጠፋፋት ቀን ከሌሊት መስራት ብቻ ሳይሆን ሲያልሙም እንደነበር ለመገመት መመራመር አይፈልግም አሁን በሃገሪቱ የተለያየ ቦታዎች የሚታየው ውጥረት መስካሪ ነው. ዛሬ ሀገሪቱ በሁሉም ቦታዎች ማለት በሚቻል መልኩ ከግለሰብ እስከ ቤተሰብ ከቤተሰብ እስከ ማህበረሰብ ስፍር ቁጥር የሌለው ጥያቄዎች እንዲያነሳ ተገደዋል ለዛም ነው ሲኖዶሱም ሆነ መጅሊሱ ፣ አማራው ኦሮሞው ጉራጌው ደቡቡ ሌላው ቀርቶ መጣሁለት የሚሉት በአንድ ወቅት  አንኳን ካንተ ተፈጠርኩ ያሉት የትግራይ ህዝብ ሳይቀር ጥያቄ አለው.


ማንዴላ ደም ማፋሰስን ያስቀረ የሰላም መምህር 
ከ400 ዓመት በላይ ዚገዛ ሲረገጥ የነበረ ሕዝብ ስቃዩና ሞቱን ብቻ ሳይሆን ብዙዎች የፈሩትን ደም መፍሰስና እልቂት በብልህ መሪነታቸው አገሪቱን ከመዓት ህዝባቸውን ከእልቂ ታድገዋል ለዚህም የኖቬልን ሽልማት አለም ድስ እያላት ሰጥታዋለች ደም አለማፍሰስ ቀላል ቢሆኑም ሰዎች ደም እንዳያፈሱ ማድረግ ግን የማንዴላን ማንንት ያስመሰክራል. ማንዴላ ለአፍሪካ ብቻ ሳይሆን ለአለም ሰላምን ያስተማረ የሰላም ወንጌላዊ ነው.  

መለስ የብዙዎቹ ህይወት ያጠፉ የሞት መልክተኛ ነበር
ጦርነት ውስጥ መግደልም መሞትም ያለ ነው ሰላማዊ ዜጋን ከሃውዜን ጀምሮ እስከ 1997 ሚያዝያ ድረስ በርካታ እልቂትን የፈጸመ ያስፈጸመ ህዝብን በጅምላ ከጨረሱ ነፍሰ ገዳዮች ጋር የሚመዘገብ ነፍሰ ገዳይ ነው.ቻው ቻው ጦርነት ባሉን  ማግስት በ100ሺ የሚቆጠሩ ወጣቶችን በባድሜ አስጨርሶ በሱማሌ የወንድሞቻችን ሬሳ በመንገድ ሲጎተት ተመልክተናል. ለዚህ ሁሉ ህይወት መጥፋት ክመለስ በላይ ተጠያቂ አይኖርም የርሳቸው አና በዙሪያቸው ያሉ ደም ጠገብ ወታደሮች እና ለሆዳቸው ያደሩ ስግብግቦች ልጆቻቸውን በአውሮጳ እና በአሜሪካ እያኖሩ የድሃውን ልጅ በበረሃና በጫካ የጥይት ቀለብ አድርገውታል. ጦርነት እና ረሃብን አምልጦ የወጣውም ዜጋ ቢሆን በየባህሩ እና በየበረሃው እንዲሞት ያደረገው የመለስ ፖሊሲ ለመሆኑ ማስረጃ አያሻም ከየትኛውም ጊዜ በተለየ ሞት የረከሰበት ስርዓት ዘርግቶ ያለፈ የሙት መንፈስ መሪ ነበር ማለት በጥሩ ሁኔታ ይገልጸዋል.

ማንዴላ የይቅርታ አባት ነበር.
ማንዴላ ለ27 አመት የታሰረው ለፍትህ ፣ ለነጻነት እና ለእኩልነት ነበር. ከእስር ከወጣበት ጀምሮ ሀገሩን አንድ ለማደርግ በነጮች ሲረገጥ ለቆየው ጥቁር የሃገሩ ዜጎች ፍቅርና ይቅርታ በማስተማር የዛሬዋን የአፍሪካ ታላቅ ሃገር ደቡብ አፍሪካን አንድ ያደረገ ታላቅ አባት ነው። የማንዴላ የይቅርታ ልብ ባይኖር ኖሮ  ከእድሜው 1/4 በእስር ቤት ያማቀቁትን ወገኖቹን ካሉት በታች ከሞቱት በላይ  አድርገው ላኖሯቸው ፣ ሴቶቻቸውን ደፍረው ወንዶቻቸውን አስረው ገለው የቀሩትን ያሰደዱትን ጨካኝ እና አረመኔ መሪዎችን ይቅርታ ማድረግ ብቻ ሳይሆን በጠርጴዛ ዙርያ ተቀምጦ ከሱ በኃላ ላለው ትውልድ ይቅርታ ምን ማለትን በወሬ ብቻ ሳይሆን በተግባር ያረጋገጠ ድንቅ የክፍለ ዘምኑ ስጦታ ነብር.

መለስ የበቀል አባት ነበር
የመለስ የፖለቲካ አባት የሆኑት አቦይ ስብሃት ከነገሩን ብንጀምር  አማራና ኦርቶዶክስን ሰበርነው ያሉት በውስጣቸው ያለውን የበቀል ስሜት የሚገልጽ ነው. ለምን እንደሆነ ባይገባኝም በቀላቸውን የጀመሩት አብረዋቸው ጫካ ከወጡት ሲሆን በመቀጠል የበቀሉ ተጋፋጭ የነበሩት  ጭቁኑ  የትግራይ ህዝብ እንደነበሩ አብረዋቸው ለትግራይ ሕዝብ በእርዳታ የመጣን ስንዴን ሸጠው የብሉ በተደጋጋሚ ጽፈው አንብበናል በመቀጠል የበቀሉ ቀማሽ የሆነው መላው ህዝብ ነው. ባንኮቹ ሲዘረፉ ፣ ትምህርት ቤት ሲቃጠል ፣ የፍትህ ሰዎቹ በየአደባባይ ሲረግፉ ፣ በቀሉ ከቀን ቀን ሲጎነጨው ኖሯል ፣ አቶ መለስ አስከሞቱባት ሰዓት ድርስ ሀገራቸወና ህዝባቸውን ሲበቀሉ የበቀል አባት ነበሩ.    

ማንዴላ ስልጣንን ሳይፈልግ የወሰደ ፈቅዶ የመለሰ
ሰዎች ስልጣንን ፈልገዋት ሲሮጡ ብንመለከትም እንደ ማንዴላን ግን ስልጣን ፈልጋቸው ነበር ያገኘቻቸው.  ድቡብ አፍሪካውያንን የሚያድን ስልሆነ ተለምነው ወደ ስልጣን የመጡ መሪ ብቻ ሳይሆኑ ስልጣንን በፍቃዳቸው አስረክበው ያልጦርነት ስልጣን የማይገኝባት አፍሪካን አዲስ ታሪክ ጽፈውባታል.ዛሬ ጥቂትም ቢሆኑ ሌሎች የአፍሪካውያን መሪዎች የማንዴላን ሌጋስ እያራመዱ ነው.

መለስ በስልጣን ጥም ያበደ የስልጣን ጥመኛ
በስልጣናቸው የመጣን ሁሉ ሲያሳቸው በአደባባይ ሲያሻቸው ደግሞ በጓሮ አልያም በሰው እጅ ሲያስጠፋ የኖረ መሆኑን የማይደበቅ አውነት ነው. ፓርቲያቸወንም ሆነ ሀገሪቱን  ለብቻቸው ስልጣኑን እሳቸውን በዞሩበት ሲያሻቸው ፕሬዝዳንት አልያም ጠቅላይ ሚንስተር እያሉ እንደ ጽጉር ቤት ወንበር በዞሩበት ስልጣን ማዞሩን ከራሽያው ፑቲን የተማሩ እስኪመስልባቸው ድረስ ሲጠቀሙበት አይተናል. ስልጣናቸውንም ልብቻቸወ ይዘወት እንደነበር ላማውቅ ከተፈለገ አሁን ያለውን መንግስታዊ መዋቅር መመልከት በቂ ነው. በአቶ መለስ ጊዜ ያልነበረ አገርን በጋራ መራት በሚል ፈሊጥ አቶ ኃይለማርያምን እንደ ጋሪ ፈረስ እንዲጎተቱ አድርጓቸዋል ዛሬ የአቶ ኃይለማርያም ስልጣናቸው ከአቶ መለስ ጋር መቃብር የወረደ እስኪመስል ድረስ በሃገሪቱ ማንኛውም ጉዳይ ላይ እንኳን መወሰን ይቅርና መደራደር እንደማይችሉ የሳቸውን ውሳኔ  ማንም ተግባራዊ እንደማያደርገው በተለያየ አጋጣሚ ታዝበናል. በቅርቡ እንኳን ለአውሮፓውያን መልክተኞች ቃሊትን እንዲጎበኙ ከፈቀዱ በኃላ በቃሊቲ ባለስልጣናት መከልከላቸውና ግራ ማጋባት ብቻ ሳይሆን አገሪቱን እነማን እና እንዴት እንደሚመሯት የማይታወቅበት የአቶ መለስ ሌጋሲ እንደሆን ለመረዳት ችለናል.

ማንዴላ ታሪክን ሰርቶ ያልፈ ሲተረክለት የሚኖር
ዛሬ የማንዴላ ታሪክን ለመተረክ በአለም ዙሪያ ማንዴላ የረገጣቸው ቦታዎች በሙሉ አሻራቸውን ለመጪው ትውልድ ትተውበት አልፈዋል በሚል ተከብረውና ተጠብቀው እንደሚኖሩ ማናችንም አንጠራጠርም.ደቡብ አፍሪካ ብቻ ሳትሆን ዓለም ባንዲራዋን ዝቅ አድርጋ ትሸኛቸዋለች የአለም የሚዲያ ማሰራጫዎች የማንዴላን ታሪክ ሲያወሱና ሲዘግቡ ጊዚያቸውን ሰጥተው ሲያስተላልፉ እንደሚሰነብቱ ጥርጥር የለኝም.በርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ግን ማንኛችንም የኝህን ትልቅ ሰው ታሪክ  አውርተንም ሆነ ጽፈንም እንደማንጨርሰው የታወቀ ነው. የማንዴላ ታሪክ ታሪክ ብቻ ሳይሆን እውነተኛ ገድልም ጭምር ነው. ገድላቸው ለአፍሪካ, ለአውሮጳ, ለኤዥያም ሆነ ለላቲን አንድ ትምህርት የሰጠ ወጥና ማንም ሊያቆሽሰው የማይችል እውነት ነው.

መለስ ታሪክን ያጠፋ በታሪክ ተጠያቂ
ለብዙ ሺ አመታት ጀግኖች የወደቁላትን ሀገር ታሪክ አልባ አድርጎ ያስቀረ የዝህችን ብርቅዬ አገር ታሪክ በራሱ እድሜ የለካ ደካማ ቀን ሲመጣ ታሪክ የሚወቅሰው ዘረኛ በስጋ ለመጠየቅ ሳይበቃ ቢያልፍም ሙት ወቃሽ  አታድርግኝ እያልን እንደምንወቅሳቸው እሙን ነው. መለስ ታሪክን ያጠፉ ብቻ ሳይሆኑ በታሪክ ውስጥ የጠፉ መና የቀሩ ህልማቸው ባዶ ውስጣቸው ቆሻሻ ነው. ክብራቸውንም በነውራቸው የሸፈኑ ሃፍረት የማያወቃቸው ከራሳቸው አልፎ ለልጅ ልጆቻቸው ሃፍረትና ውርደትን ትተው አልፈዋል ከማንም በላይ ታሪክ የመስራት እድል የነበራቸው ቢሆንም ተሸማቀው እድሚያቸወን በከንቱ ያሳልፉ ከድሃው አፍ ላይ የሰበሰበውን ሳይበላ በስቃይ ላይመለስ የሄደ ወራዳ ነው.




No comments:

Post a Comment