አፍሪካ የነጻነት አባቷን አጣች !
የኔልሰን ማንዴላ ሞት ለአፍሪካ ብቻ ሳይሆን ለመላው አለም የሃዘን ቀን ነው. ማንዴላ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የአንድነት ፣ የመቻቻል በአጠቃላይ የመልካም ነግር ምሳሌ ናቸው.በምድራችን ተልዕኳቸውን በሚገባ ፈጽመው ከሄዱ ሰዎች ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው. ለሕዝብ ተፈጥረው ለሕዝብ የኖሩ ምርጥ እና ድንቅዬ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ሰጦታ ነበሩ. የ27 አመት የእስር ቤት ስቃይና መከራ ሳይበገር ዘረኞችን ድል ያደረገ ጀግና ነበር. እንደ አፍሪካ መሪዎች ለስልጣን ሳይስገበገብ አለም ከአፈሪካ ያላየውና ያለሰማውን ስልጣንን በፈቃድ የመልቀቅ ቆራጥነት የተሞላበትን እውነተኛ ዲሞክራሲን ለብዙዎች ያስተማረ ድንቅና ብርቅዬ አባታችን ነበር. ሕይወት ገደብ አላት ያለገደብ የሚኖር ማንም የለምና ማዲባም ግዳጁን ተወጥቶ ላይመለስ ቢሄድም ከብዙዎች ህሊና በቀላሉ አይጠፋም.
አለመታደል ሆኖ አፍሪካውያን በጠቀላላ ማለት በሚቻል መልኩ ለመሪዋቻችን ሞትን ጥፋትን ብንመኝም ለማዲባ ግን ረጅም ዕድሜና ጤናን ስንመኝ ኖረናል ይሄ ደግሞ ከምንም የመጣ አይደለም ለታላቁ አባት ካለን ክብር የተነሳ ነው. 3/4 የሚሆኑት መሪዎቿ ከ20 አመት በላይ ስልጣናችውን ሳይለቁ ከፊሎቹም ለልጆቻቸው ለዘመዶቻቸው አስተላልፈው በሚኖሩባት አፈሪካ የተገኙ ምርጥ መሪ ፣ የአፍሪካ የቁርጥ ቀን ልጅ ነበሩ. ምንም እነኳን ለደቡብ አፍሪካ የመጀመርያው ጥቁር መሪዋ ቢሆኑም ለ5 አመታት ከ1994 - 1999 አገራቸውን መርተው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ያደረጉ አንበሳ መሪ ነበሩ ምናለ ከነዚያ ስግብግብ የአፍሪካ መሪዎች እድሚ ወስዶ ትንሽ እድሜ በጨመረላቸው የሚሉ በርካቶች እንደሆኑ አምናለሁ.
ለማንኛውም ማንዴላ ጥሩ ስራን ሰርተው አልፈዋል በሕይወታቸው ካደረጉተ ያልተማራቹ መሪዎች ሆይ ዛሬም ጊዜ አላቹ ቆም በላቹ ተመልከቱ ዘላለማዊ ሰው የላም እንኳንስ እናንተ በሰው ደም የጠገባቹ ፣ ሚሊዎኖችን በረሃብ ፣ በጦርነት የመታሰቃዩ ሰው በላዎች ይቅረና ማንዴላም አልፏል.ስራው ግን በሚሊዮኖች ሲወሳ ይኖራል ታሪክ ሲዘክረው ከትውልድ ትውልድ ሲዘከር ይኖራል. በየትኛውም ተውልድ የማይፋቅ የነጻነት መብራት ለኩሶ አለፈ.
የማንዴላ ልጆች በአባታቸው የተነሳ ሲሞገሱና ሲከበሩ ይኖራሉ የሆዳሞቹ ለጆች ደግሞ ሲሳደዱ ሲሸማቀቁ ይኖራሉ. ሆዳሞች ሁሌም ራስ ወዳዶች ሰለሆኑ ከነሱ በኃላ ስለሚመጣው ትውልድ ዴንታ ቢሶች ናቸው. ዘሬ የሚያደርጉት ለነገ ትውልድ ጠንቅ መሆኑ ጠፍቷቸው ሳይሆን መሰሪዎች በመሆናቸው ነው. እንደ ማነዴላ ትውልድን አቀራርቦ ማለፍ ሲገባቸው በዘር በሃይማኖት ከፋፈለው ትውልዱ ጥላቻን አዝሎ እነዲኖር ቀን ከለሊት ይሰራሉ. ማንዴላ ነጭ ከጥቁር ሲያቀራርብ የኛ መሪዎች ደግሞ ለዘመናት አንድ የነበረን ጠውለድ በጎጥ ከፋፈለው እንደ ጠላት እንዲተያይ በዓይነ ቁራኛ እንዲጠባበቅ የማይፈታ ሰንሰላት በአንገቱ አጥልቀውለት መጣልህ ሲባባል እነዲኖር አስገድደውታል. ይህም ቀን ያልፍና የራሳችን ማንዴላ እንዲመጣ የዘወትር ምኞቴ ነው. ማን ያውቃል አኛም በህይወት እያለን መሪዎቻችን በህዝብ ተመርጠው ለህዝብ ኖረው ሲያልፉ እናይ ይሆናል.
የማንዴላን ነፍስ አምላከ በገነት ያደረግ! ለቤተሰቦቹ ፣ ለወዳጆቹ ፣ለሚወዱትና ለሚያደነቁት ሁሉ አምላክ መጽናናትን ይስጥ.
No comments:
Post a Comment