Friday, December 20, 2013

መርካት

ካት


እንደምንመገበው ምግብ ወይም የምንጠጣው መጠጥ ልንረካባቸው የማንችላቸው ነገሮች በረካታ ናቸው. መረካት ፈረንጆቹ satisfaction የሚሉት ቃል በህይወታችን ሙሉ አብረውን ከሚኖሩ እና እኛነታችንን ለመለካት ከሚያስፈለጉን ወሳኝ መመዘኛዎች አንዱና ዋናው ነው. ማናችንም ብንሆን በመርካት እና ባለመርካተ መካከል ስንዋዥቅ ነበርን አለን ወደፊትም እንኖራለን. በዓለማችን የሚከሰቱ ሂደቶች በሙሉ ያለመርካት ውጤቶች ናቸው ማለተ ይቻላል. የሰው ልጅ ኑሮውን የተሻለ ለማድርግ አስቦ ተጨነቆ የፈጠራቸው የዘመናችን ቴክኖሎጂም በዚሁ ውስጥ ይካተታሉ. እራስን ለማሸነፍ ኑሮን ለመለወጥ የሚድረግ ግብግብን ከዚህ ጋር ይገናኝ አየገናኝ ለማወቅ ነገሮቹን ከብዙ ጎኑ መመልከት ተገቢ ይሆናል.

በስደት በቆየሁባቸው ትንሽ የማይባል አመታት ውስጥ ስደት ካስተማረኝ በርካታ ትምህርቶች አለመረካት የመጀመሪያ ቦታ ይይዛል. ከተለያዩ አህጉራት አፍሪካ አውሮጳ እስያ እና አሜሪካ ከመጡ ዜጎች ጋር የመስራትም ሆነ የመኖር አጋጣሚ አግኝቼ ነበር. ሁላቸንም ላይ የምመለከተው ያለመረካት ምክንያት ከምን እንደሚመጣ ማወቅ በጣም አስቸጋሪ ነበር. መጤነታችን ይሆናል ብዬ ያሰብኩበትም ጊዜ ነበር. ቢሆንም ግን ትክክል አይደለም. ከኛ ውጪ በደረሰኩባቸው አገሮች ዜጎችም ቢሆን መጠኑ ይለያይ እነጂ ሁሉም ህብረተሰብ ጋር አብሮ እንደሚኖር ታዝቢያለሁ.

አገር ቤት ያለው ሱዳን ቢወጣ ሱዳን ያለው አረብ አገር ቢወጣ አረብ አገር ያለው አውሮጳ ቢውጣ አውሮጳ ያለው ደግሞ አሜሪካና ካናዳ ቢደርስ ምኞቱ አብቅቶ እርካታን የሚያገኝ የሚመሰለው ወገኔ ቀላል አይደለም. ይህን ሃሳቤን የሚጋሩ በረካታ ወንድሞችና እህቶች እንዳላችሁ አውቃለሁ. እዚህ ጋር ሳልጠቀስ የማላልፈው ነገር ቢኖር ጥቂቶችም ቢሆኑ ባላቸው እየተደሰቱ የሚኖሩ እንዳሉ እሙን ነው. በርግጥ ህይወትን ወደፊት ለማሰኬድ በጎ በጎውን መመኘት ተገቢ ነው. ይሁንና አስረግጬ መናገር የምፈልገው እውነታ ግን ማንም ሰው ፈልጎም ይሁን ሳይፈለግ የሚያገኘው አይደለም.

ስደት በማንኛውም መልኩ በጎ እና የሚደገፍ አይደልም ዛሬ 2005 IOM (International Organization for Migration) ባውጣው መረጃ መሰረት በመላው ዓለም  200 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ በተለያየ ምክንያት ወደ ስደት ገብቷል ይሄ ቁጥር በየአመቱ በሚያስፈራ መልኩ እየጨመረ ይግኛል. ህይወት አጭር ናት መጽሐፍ ቅዱስ የሰው እድሜ ቢበዛ 70 ነው ይላል ብዙዎቻችን ኑሮን ሳናጣጥማት ሳንረካ በስደተ እንደተንከራተትን እኖራልን አንዳንድ ተመራማሪዎች በቃኝ አለመርካትን ከበሽታም ይወግኑታል ብዚህም ተባለ በወድያ ባልን እና በተሰጠን አመስግነን መኖርን መልምድ ይግባናል በርግጥ ይህ ማለት ባልንበት ቆመን መቅረትይገባል ማለት አይደለም የሰው ልጅ ማድግ መለወጥ የግድ ይለዋል። ሁሌም ቢሆን ወደላይ እያንጋጠጡ የሌላውን መመልከት ተገቢ አይደለም ወደ ታች ዝቅ ብለው ከኛ በታች የሚኖሩትንም መመልከት ተገቢም አስፈላጊም ጭምር ነውጫማ የለኝም ብለህ አታማር እግር የሌለው አለናአይደል የሚባለው. ባለን ነገር አለመርካት በርካታ ችግሮችንም ይዞብን እንደሚመጣ መዘንጋት የለብንም የሌለንን ነገር በመመኝት ከምናጠፋው ጊዜና የአእምሮ ጭንቀት ሌላ ወዳልተፈለገ የህይወት መንገድም ይመራናል ዋናው መመልከት ያለብን የመኖሪያ ቦታችንን ሳይሆነ የምንኖርበትን ሁኔታ ነው ፍጣሪ ለኛ ያዘጋጀወን ሁሉ በጊዜው ያደርገዋል. ሁላችንም እንደየ እምነታችን ወደ ፈጠረን አምላክ ፊታችንን ማዞር ተገቢ ነው ያን ጊዜ ፍጹም የሆነ እርካታ እንደምናገኝ እርግጠኛ ነኝ። ይህን የምልበት ምክንያት የሰው ልጅ ወደ ፈጠረው መመልክት ሲጀምር ለምን እንደተፈጠረ መገንዘብ ይጀምራል ያን ጊዜ ማመስገን ይጀምራል ማመስገን ደግሞ እርካታን ያመጣል አለማችን ከተፈጠረችበት ሰዓት ጀምሮ ሃብታምና ድሃ ገዥ እና ተገዢ መሪና ተመሪ ስታስተናግድ ኖራለች አልረካ ያለ ሌላውን እየረገጠ ማለፉ የማይቀር ነው አለመርካት ከትንሽ ተነስቶ እያደገ እንደሚሄድና መጠፋፋትንም ያስከትላል ለሰው ልጅ ከምንም በላይ ሰላም እና ጤና ዋናው ነው ወንድሞቼ ፍጣሪ ፈጣሪ በያለንበት ሰላምና ጤናውን ያድለን የተቀረው ሁሉ በጊዜው ይሆናል በተቻለን መጠን ባለን መርካትን መልመድ ተገቢ ነው

አምላክ ሀገራችንን እና ሕዝቧን ይጠብቅ